የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

home

እምቢ ለአፋኝ ወታደራዊ አገዛዝ፤

 የሽግግር መንግስት አሁን ይቋቋም !! 
ሸንጎ ሕወሃት መራሹ የኢሕአዴግ መንግስት ያወጀውን ቀጥተኛ ወታደራዊ አገዛዝ እጅግ በጣም አጥብቆ ይኮንናል። አፋኙ ስርዓት አሁንም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ማፌዙን አላቆመም፤ አንድም ሕዝባዊ እንቅስቃሴው ባሳረፈበት ምት ተደናግጦ ግራ ስለተጋባ የሚይዘውና የሚጨብጠው ጠፍቶታል፤ አንድም እንደቀድሞው መግዛት እቀጥላለሁ በሚል ቅዠት ውስጥ እየዳከረ ነው። ትናንት ብሄራዊ መግባባትን አመጣለሁ ብሎ ከወተወተ በኋላ ጥቂት እስረኞችን ለቆ፤ ህዝቡ በደስታ ፈንድቆ ሲጨፍር የረገጠው ሳር እንኳን ቀና ሳይል፤ በማግስቱ ጠቅላይ ሚንስትር ተብየው ከስራ ተሰናብቻለሁ አሉ፤ እንዲሁም ከአንድ ቀን አዳር በኋላ ኢሕአደግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጌለሁ አለ። 

Hits: 31

ለፍትሕና ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል ይቀጥላል

 
 
የኢትዮጵያ ህዝብ የግራ ትግል ሸንጎ በነአቶ በቀለ ገርባ፤ አንዱአለም አራጌ፤ እስክንድር ነጋና በሌሎችም እስረኞች መፈታት የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን። ለቤተሰቦቻቸው፤ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ደስ ያለን እንላለን። 
አሁን የምናየው ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ ለአመታት ያደረገው ትግል ያስገኘው ተጨባጭ ውጤት ነው። ። ይህ ውጤት የተገኘው ከፍተኛ መስዋእትነት የተከፈለበትን ፈታኝ ትግል በጽናት በማካሄድ እንደሆነ ስናወሳ፤ አሁን ከእስር የተለቀቁት ታጋዮች ያሳለፉት ሰቆቃ ለዚሁ ትግል የተከፈለ ዋጋ መሆኑን እንረዳለን። ከዚህም ባሻገር ለዚህ ድል እውን መሆን ህይወታቸውን ለሰጡ፣ ለታሰሩ፣ ለተሰደዱና ለተሰቃዩ ታጋዮችና ቤተሰቦቻቸው ሁሉ የሚሰማንን ዘላላማዊ ክብር መግለጽ እንወዳለን። 

Hits: 44

ሕዝብን በመጨፍጨፍ ትግሉን ለመቀልበስ አይቻልም!

ሰሞኑን ወልዲያ የአመፅ ዓውድማ ሆና ሰንብታለች። የጥምቀትን በዓል ተንተርሶ በተገኘው ቀዳዳ በሰሜን ኢትዮጵያ ከተሞች ውስጥ ሕዝቡ በአገዛዙ ላይ ያለውን ተቃውሞ ሲገልጽ ውሏል። በትክክለኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ደምቀው የዋሉት ወልድያ፣ ባህርዳር፤ ጎንደር ለዚህ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ። በወልድያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በአገዛዙ የፀጥታ ኃይሎችና በወጣቶች መካከል ግጭት አስከትሎ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል፣ ንብረትም ወድሟል። ሸንጎ በሰው ሕይወት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን መሪር ሃዘን ለወጣቶቹ ወላጆችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይገልጻል

 

PRESS HERE TO READ MORE

 

 

 

 

Hits: 169

የሶስቱ ድርጅቶች የጋራ መግለጫ

Hits: 117

መፍትሄው በብሄራዊ መግባባት የሽግግር ሂደትን እውን ማድረግ እንጂ ለ27 ዓመት የተደረገውን መድገም አይደለም

በትላንቱ ዕለት ህወሓት-መራሹ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ 17 ቀናት የወሰደ ስብሰባውን እንዳጠናቀቀ በማመልከት መግለጫ አውጥቷል። ስብሰባው ከመጠናቀቁ በፊት ትልቅና አዲስ ነገር አመላካች የሆነ ውሳኔ እንደሚያሰተላልፍ በተለያየ መልክ ሲጠቁም ቢከርምም፣ የመጨረሻው መግለጫ እንደሚያመለክተው ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ካለፉት ጊዜያት የተለየ ተስፋ ሰጭ ነገር ይዞ አልመጣም።

Press here for more

Hits: 302