የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

አባይን ለመንከባከብ የጎሰኛነት አገዛዝ በዲሞክራሳዊ አገዛዝ መተካት አለበት

Rate this item
(0 votes)

ከ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ

........የዓለም ውሎች የአፍሪካን ተፋሰስ አገሮች መብት የሚደግፉ ከሆኑ ግብፆች ከሕግ በላይ ናቸው ማለት ነው? በእኔ ግምት ከዓለም ሕግ በላይ አይደሉም። በግድቡ ምክንይት ውሃው ይቀንስ አይቀንስ፤ ከግድቡ የሚገኘው ጥቅም ከጉዳቱ ከፍተኛ ይሁን አይሁን ገና አይታወቅም። ሁለቱ መንግሥታት የተለያዩ ማስረጃዎች ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የግድቡ ማህበራዊ ጥቅምምን እንደሆነ፤ አካባቢውንና ነዋሪዎችን  እንዴት በዘላቂነት እንደሚጠቅም/ እንደ ማይጎዳ፤ የመብራት ኃይሉን ሽጦ የሚያገኘውን የወጭ ምንዛሬ የት ላይ እንደሚያውል ወዘተ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በግልፅና በአስቸኳ ማስረዳት አለበት። ማስታወስ ያለብን፤  ግብጾችና  ሱዳኒሶች ከእንግሊዞች ጋር በመተባበር የአባይን ወንዝ ለልማታቸው ሲገድቡ (አስዋንና ሮዘሪስ) ማንንም የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች ጥቅምና ፍላጎት ዋጋ አልሰጡትም። ግድቦቹ የጥቁር አፍሪካ አገር ሕዝቦችን ይጎዳል፤ አይጎዳም ብሎ የጠየቀ ታዛቢ አልነበረም።  ከዚህ ባሻገር፤ ኢትዮጵያ በግዛቷ ውስጥ ግደብ መስራቷ ለግብፆች ስነ-ልቦና፤ ጉራና የታላቅነት መለያ፤ ማለትም፤ አባይን በበላይነት መቆጣጠር የለመዱት ባህል ይናዳል የሚል ስሜት አለ። ድሃ፤  ኋላ ቀር፤ ድምፅ የለሽ፤ ጥገኛ ወዘተ የነበሩ የጥቁር አፍሪካ ተፋሰስ አገሮች ወንዞችን የመጠቀም መብት አለን ብለው በጋራ ሲቆሙ፤  ግብጾች ይህ ሂደት የማይቆም ጉዳይ መሆኑን አይተው፤  አፍሪካ እየተለወጠች  መሄዷን አልተቀበሉትም። ኢትዮጵያና ሌሎች የጥቁር አፍሪካ  አገሮች ኢኮኖሚዎች ያድጋሉ ብሎ የገመተ ግብጻዊ የለም።  በአብዛኛው የግብፅ መሪዎች ለጥቁር ሕዝቦች  ንቅት ያሳያሉ ማለት ነው። ትህትና፤ ይሉኝታ፤ እኩልነት ወዘተ አሳይተው አያውቁም። በአፍሪካ አህጉር ተቀምጠው አፍሪካዊ ነን ብለው አያውቁም። ይኼን ዶሓ አይቸዋለሁ። ምንም እንኳን “መለስ እኛ አረቦች ነን” ቢልም፤ በዚህ በኩል እኛ ም  ኢትዮጵያዊያን ጥቁር አፍሪካዊያን  ሆነን ከጥቁር አፊርካ ጋር የጠበቀ ግንኙነት አልመሰረትንም። ለራሳችንና ለሃገራችን ስንል፤ የአባይን መብት ለማስጠበቅ ጭምር፤ የጠበቀ ሁለ-ገብ ግንኙነት መመስረት ግዴታ ነው።................ሙሉውብ ለማንበብ ይህን ይጫኑ