የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

selamawi

ለሰላማዊ ሽግግር የሸንጎ ራዕይ

 

ጥቅምት 12 ቀን 2009 ዓ.ም

ኢትዮጵያ አገራችን ከፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ተማግዳ የቆየችበት ወቅት ገደቡን አልፎ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለመውለድ በቅቷል። በሙስሊም እምነት ተከታዮች፣ በኦሮሞ ክልል፣ በአማራው ክልል በጎንደርና ጎጃም የተቀሰቀሰውና የተቀጣጠለው ሕዝባዊ እምቢተኝነት የዚሁ ነጸብራቆች ናቸው።

የህወሃት መራሹ የኢሕአዴግ አገዛዝ እንዳለፈው ሁሉ ያረጀ ያፈጀ የ25 ዓመት ስልቱን፣ ሃይልና ጭካኔን በመጠቀም ሕዝባዊ እምቢተኝነቱንና አመጹን ለማፈን ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ደረጃ የሞት የሽረት እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል። የሕዝቡ ትግል ግን እየከረረና እየተጠናከረ እንጂ እየተዳከመ አልመጣም። ይህ አዲስ ክስተትና አዲስ የፖለቲካ አካሄድ መጣኝ የሆነ ምላሽን ይጠይቃል። ይህንንም አዲስ አካሄድና አቅጣጫን ለመንደፍ ሁሉም የሚሳተፍበት የፖለቲካ ሂደት መወጠን ከምን ጊዜውም በላይ በጣም አስፈላጊ ነው። ከዚያ ውጭ ግን የህዝብን ጥያቄ በተለመደ መልክ አፍኖ ለመቀጠል መሞከር የበለጠ ትርምስና አቅጣጫውን መገመት ወደሚያስቸግር ቀውስ የሚወስድ ይሆናል።

በሚያሳዝን ሁኔታ አምባገነኖቹ መሪዎች ከተጠናወታቸው የክህደትና የጨለምተኝነት ባህሪ የተነሳ ያለውን ዕውነታ መገንዘብና መረዳት ተስኗቸው የሕዝብን ተቃውሞና የለውጥ ፍላጎት በአግባቡ ለማስተናደግ የፖለቲካ ፍላጎትም ሆነ ብቃት አይታይባቸውም። ይህንን ማየት ቢችሉ ኖሮ ያለፉበትን መንገድና የሕዝቡን ጥያቄ ባጤኑና በጎ ምላሽም በሰጡ ነበር።

የ2005 ብሔራዊ ምርጫን ተከትሎ የተከሰተው እልቂትና ጭፍጨፋ በሽህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ለሞት፣ ለእስራትና ለስደት በመዳረግ የልዩነቱ ደረጃና ጥልቀት ጎልቶ የታየበት ሲሆን፣ መንግሥት ተብየው ቡድን ግን ለሥልጣኑ ሟችና ለሕዝብ ፍላጎት ግደቢስ መሆኑን በወሰደው እርምጃና በመረጠው መንገድ በገሃድ አረጋግጧል። የተከተለውንም አጥፊ አቅጣጫ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሎበት በተወሰነም ደረጃ ቢሆን የተቃዋሚ ድርጅቶችን ለማሽመድመድ ችሏል። አሁንም የሚጓዝበት መንገድ ከዚያ ቢብስ እንጂ የተለዬ አይደለም። የነጻ ሚዲያ ዘርፎችን አፍኗል፣ ነጻ የሆኑ የሙያና የመብት ተከራካሪ ድርጅቶችን ዘግቷል፣ “የጸረ ሽብርተኝነት” የሚል ሕግ አውጥቶም ከሱ ጋር ያልተሰለፉትንና የሚቃወሙትን ሁሉ አጥቅቶበታል። ይህም አድራጎቱ ሲሰብክ የነበረውን የመድብለ ፓርቲ ልፈፋ ባዶነትና የኢዴሞክራሲያዊነት ባህሪውን አጋልጧል። በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስምና ልማታዊ መንግሥት በሚል ካባ ታጅሎ የሚያጭበረብር ብቸኛ የሥልጣን ባለቤት መሆኑን በገሃድ አሳይቷል። በዚህም አካሄዱ የሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በርን በመዝጋቱ አሁን ወደምንገኝበት ሕዝባዊ ሰላማዊና ትጥቃዊ እንቅስቃሴዎች በየቦታው የተስፋፋበት ወቅት ላይ ተደርሷል። አገዛዙ በበኩሉ ይህንን ሕዝባዊ ተቃውሞና የለውጥ ፍለጋ ትግል ለመቆጣጠር የሃይል እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል። ውጤቱ ግን ይበልጥ ስርዓቱን ከድጡ ወደማጡ ከመሄድ አላዳነውም። .......ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ