የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ [ሸንጎ] ኦፊሴላዊ ድረ ገፅ

yegara3

ኢትዮጵያውያንን በዘር ከፋፍለው የሚያፋጁንን ጎሰኞች በአንድነት ተነስተን “በቃችሁ” እንበላቸው!!!

አሁን ኢትዮጵያውንን የገጠመን ችግር ድንገተኛ አይደለም። ችግሩ ሰፊ፣ ከባድ፣ ለበርካታ ዓመታት በፀረ-ኢትዮጵያ ባዕዳንና አገር-በቀል የጥፋት መሣሪያዎቻቸው ጥምረት በገፍ እንድንጋተው ከተጠመቀልን መርዝ ገና ገፈቱን ነው እየቀመስን ያለነው። አንዱን ብሔረሰብ በሌላው ማስፈጀት የተጀመረውም ዛሬ አይደለም። ሕወሓት እስከዛሬ በሥልጣን ላይ ለመቆየት የቻለው ኢትዮጵያውያንን በቋንቋ የሚከፋፍል ‘ሕገ-መንግሥት’ አዘጋጅቶ በግድ በሕዝቡ ላይ በመጫን፣ በዕቅድና በስልት፣ ብሔረሰቦችን በሰበብ-አስባቡ እየነጣጠለ፣ እያናቆረ፣ እያጣላ፣ እያጋደለ፣ እንደሆነ ለአንድ አፍታም ልንዘነጋው አይገባንም። ይህንን ዛሬ በስፋት እየታየ ያለውን፣ ከኢትዮጵያውያን ፍፁም የማይጠበቅ፣ በብሔረሰቦች መኻል የእርስ-በርስ መጠፋፋት ለማምጣት ሆን ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲነጣጥልና ሲሰነጣጥቅ ነው የኖረው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚቻለው ሕዝቡን እርስበርሱ ማጋጨትና ማፋጀት ሲቻል ብቻ ነውና፣ ይህን በአዕምሮ-ቢስነት በአግባቡ ተግባራዊ እያደረገ ነው የሚገኘው!!! 
 

Press here for more